Amharic version

አሳታፊ ሶሰት አምሳያ ቀረጻ፡ መርሆችና አተገባበር (እ.ኤ.አ የ2010 እትም)

cover_page_amBy Giacomo Rambaldi
ISBN: 978-92-9081-448-1
አሳታሚ፡ የግብርናና ገጠር ልማት ትብብር ቴክኒካል ሴንተር (ሲ.ቲ.ኤ)፣ እ.ኤ.አ ሐምሌ 2010
English version | French version | Spanish version | Portuguese version

Download the Amharic version [110 pages] High resolution [73 MB].
Medium resolution [28MB]

አሳታፊ ሶስት አምሳያ ቀረጻ ማለት የአገሬውን ያአካባቢ እውቀት ከዘመናዊ የአካባቢ እውቀት ጋር በማገናኘት ራሳቸውን ችለው የሚቆሙ፣ የተመጠኑና በጂኦግራፊያዊ አቆጣጠር የተስተካከሉ ሞዴሎችን ለመስራት የሚያስችል አሳታፊ የካርታ አሠራር ነው። በአጭሩ በአገሬው የማስታወስ ችሎታ ላይ በመመስረት ፣ የአካባቢ አጠቃቀምና አሰፋፈር እንዲሁም ሌሎች ገጽታዎችን በመረጃ አቅራቢዎች አማካኝነት ሞዴሉ ላይ የተለያዩ መርፌዎችን ለነጥቦች ማመላከቻ፣ ገመዶችን መስመር ለማመላከቻ እና ቀለማቶችን ለስፋት ላላቸው ስፍራዎች ማመላክቻ መጠቀም ማለት ነው። ከዚህም በኋላ መጠኑ የተስተካከለና በጂኦግራፊያዊ አቆጣጠር የተቀመረ ሠንጠረዥ በመጠቀም ከላይ የተጠቀሰው መረጃ ለመለየትና ለማዟዟር በሚያመች መልኩ ይቀመጣል። በተራው ይህ ተለይቶ የወጣው መረጃ ይነጠልና በኮምፒዩተር ለማንበብ አመቺ እንዲሆንና ለመጠናዊ አገማመት አመቺ እንዲሆን ተደርጎ ይቀመጣል። በዚህ መልኩ የተጠናቀቀው ሞዴል በዛው በአገሬው ዘንድ ተቀማጭ ይደረግል።
አሳታፊ ሶስት አምሳያ ቀረጻ የተጸነሰው ዘመናዊውን ጂ.አይ.ኤስ. ቴክኖሎጂ በገጠር ለሚኖሩ ሕዝቦች በሚስማማ መልኩ በማቅረብ በዘመናዊ የጂ.አይ.ኤስ ቴክኖሎጂና በተፈጥሮ ሃብት ላይ ኑሯቸውን መሰረት ባደረጉና የገጠር ኅብረተሰቦች መካከል ያለውን የአቅም ልዩነት ለማጥበበ ነው።
የዚህ ማስተማሪያ ዓላማም ለጂ.አይ.ኤስና አሳታፊ ማስተማሪያ መንገዶች ተመራማሪዎችና ባለሙያዎች ጂ.አይ.ኤስን ባለሙያ ላልሆኑና ታች ላሉ ህብረተሰቦች አሳታፊ ሶስት አምሳያ ቀረጻን በመጠቀም ማዳራስ እንዲችሉ ነው። አንድ አሳታፊ የሶስት አምሳያ ቀረጻ ዝግጅትን ከመጀመሪያ እስክ መጨረሻ ለማዘጋጀት የሚያስችል ምክሮችን ደረጃ በደረጃ ያስቀምጣል። በተጨማሪም ይህንን የማስተማሪያ ዘዴ ከዚህ በፊት በተጠቀሙ ከዓለም ዙሪያ በተውጣጡ ባለሙያዎች አዋቂዎችን ስለማስተማርና ይህንን አሳታፊ መንገድ ስለመጠቀም የሰጡትን አስተያየት ያካትታል።
እ.ኤ.አ. ኅዳር 5 ቀን 2007 ዓ.ም.፣ አሳታፊ የሶስት አምሳያ ቀረጻ የአለም ጉባዔ ሽልማትን በኤሌክትሮኒክ- ባህል ደረጃ አግኝቷል። በሌላም በኩል አሳታፊ ሶስት አምሳያ ቀረጻ በአለም ከሚገኙ ተመሳሳይ መንገዶች ከምርጥ አርባዎቹ ውስጥ ተካቷል።